Home
Welcome to the Frontpage
የሐዘን መግለጫ PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Thursday, 19 February 2015 20:55

የሐዘን መግለጫ

“ነገር ግን ሰዓት ትመጣለች እናንተን የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት የሚያቀርብ ይመስለዋል“

ዮሐ ፲፮፥፪

በዕለተ ሰንበት በሊብያ ምድር በሃያ አንድ ግብጻውያን ኦርቶዶክሳውያን ላይ አይሲስ ተብሎ በሚታወቀው የአክራሪ እስልምና ሚሊሻዎች የተፈጸመውና ሰሞኑን የዓለም ሕዝብ መነጋገሪያ የሆነው አሰቃቂ ጭፍጨፋ ነው ይህን ቃል እንድናስታውሰው ያደረገን። በርግጥ ለግብጽ ምእመናን መታረድ፣ መታሠርና መቃጠል አዲስ ነገር አይደለም፤ ክርስትናን በልብና በአንደበት ብቻ ሳይሆን በሥጋቸው እጅግ የሚዘገንኑ መከራዎችን በመቀበል ሲኖሩት ዓለምም ከንፈር ሲመጥላቸው ከ1 ሺህ አምስት መቶ ዓመት በላይ አስቆጠረዋል? አይሲስ የተባለው አዲስ በቀል አክራሪ ቡድን ከዚህ በፊት በሶርያና በኢራቅ በክርስቲያንና ባላከረሩ የእስልምና ተከታዮች ላይ ተመሳሳይ ምናልባትም የከፋ ግፍ ሲፈጽም መቆየቱ አይዘነጋም። አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ ወደሌሎች አካባቢዎች የእንቅስቃሴ አድማሱን በማስፋት በክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ የሚፈጽመው ኢሰብአዊ ጭፍጨፋና አፈና የጥፋት ተልእኮው ተጠናክሮ መቀጠሉንና ያልተረዱ ሰዎች እግዚአብሔርን ያገለገሉ እየመሰላቸው የገዛ ወገኖቻቸውን እንደ በግ የማረዱን ተግባር ማደላደላቸውን የሚያመላክት ነው።

 

ዓለም ወዴት እያመራች ነው? ከርስቲያን ወገኖች እስከ መቼ ድረስ ይሆን ሳይገፉ እየተገፉ፤ ሳይበድሉ እየተበደሉ የሚኖሩት? በግፍ የሚታረዱ ወገኖችን የሚደርስላቸው ማን ይሆን? ዓለም ለክርስቲያኖች ምንም ቦታ የላትምን? ለማንኛውም እንዲህ ያለውን መከራ በጾምና በጸሎት ስለሆነ ሊዋጉት የሚገባው የዝግጅት ክፍላችን አምላክ የጥፋት መልእክተኞቹን ኃይል እንዲሽርልን የምእመናንም ስደትና እልቂት እንዲያስቆምልን በርትተን እንጸልይ የተሠዉት ወገኖቻችንና ለመከራ የተጋለጡትን ሁሉ በጸሎታችን እናስባቸው በማለት መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፤ ለግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና ለተከታዮቿ በሙሉ መጽናናትንም ይመኛል።ወስብሃት ለእግዚአብሔር

በአይሲስ አንገታቸው የተቀላው ግብፃውያን ሰማዕታት በከፊል


 

Last Updated on Thursday, 19 February 2015 21:16
 
የካርልስሩኸ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የደብር ስያሜ ተሰጠው። PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Saturday, 24 January 2015 21:42

ካስል ጥር ፲፮/፳፻፯ ዓ.ም (ጀርመን) በጀርመን አገር የሚገኘው የካርልስሩኸ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ከዚህ ወር ጀምሮ የካርልስሩኸ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተብሎ እንዲጠራ ተወሰነ። የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪም መልአከ ስብሐት የሚል የማዕረግ ስም ተሰጥቷቸዋል።


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአድባራትና የገዳማት ትክልና አመሠራረት ሥርዓትና ትውፊት መሠረት በማድረግ እያንዳንዱ ደብር ወይም ገዳም የራሱ የሆነ ስያሜ እንዲኖረው ይደረጋል።


በዚህም ምክንያት የደብሩን አመሠራረትና እየሰጠ ያለውን አገልግሎት ግምት ውስጥ በማስገባት በኢ/ኦ/ተ/ቤ የደቡብ ደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሙሴ ውሳኔ መሠረት ስያሜው እንደተሰጠም ከሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ ከመጋቤ ምሥጢር ኅሩይ ኤርምያስ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።

 

በተያያዘ ዜናም የደብሩ አስተዳዳሪ ቀደም ሲል ሲጠቀሙበት የነበረው የማዕረግ መጠሪያ ተለውጦ መልአከ ስብሐት ተክሌ ሲራክ ተብለው እንዲጠሩ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ወስነዋል።

Last Updated on Sunday, 25 January 2015 19:28
Read more...
 
የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር በአውሮፓ ተመሰረተ። PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Wednesday, 17 December 2014 10:45

የነገረ መለኮት ሩቃን ማኅበር የአውሮፓ ቅርንጫፍ

የምሥረታ ጉባዔውን አካሄደ::


ታህሳስ ፮ /፳፻፯ ዓ.ም ካስል(ጀርመን) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የነገረ መለኮት ሩቃን ማኅበር የአውሮፓ ቅርንጫፍ የምሥረታ ጉባዔውን ዳሜ ኅዳር ፳፯ ቀን ፳፻፯ .. በጀርመን ሀገር በካስል ከተማ አካሄደ በዚህ በካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በተካሄደው ጉባዔ ከጀርመን እንግሊዝ ቤልጅየምፈረንሳይ እና ሆላንድ የመጡ ፲፩ የነገረ መለኮት መሩቃን የተገኙ ሲሆን በተለያየ ምክንያት መገኘት ያልቻሉትን ጨምሮ በአጠቃላይ ፴፬ የነገረ መለኮት ምሩቃን በምድረ አውሮፓ እንደሚገኙ በጉባዔው አስተባባሪዎች የተሰበሰበው መረጃ ያመለክታል


ጉባኤው በጸሎት ከተከፈተ በኋላ የምሥረታ በዓሉን ያስተናገደው የካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበሩ ጊዜያዊ ሥራ አስፈጻሚ አባል ኾኑት መጋቤ ምሥጢር ኅሩይ ኤርምያስ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። በመቀጠልም መቀመጫውን በአዲስ አበባ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ ያደረገው ዋናው የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር በጥቅምት ፳፻ ዓ.ም. ከመመረቱ በፊት እና በምረታው ጊዜ ስለነበሩ ሂደቶች ስለ ማኅበሩ ዓላማእንዲሁም ማኅበሩ ላለፉት መታት ስላከናወናቸው በይት ተግባራት ሰፊ ገለጻ ተደርጓል። ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል። በመቀጠል ጉባዔው ቅርንጫፍ ማኅበሩን ከአውሮፓ ሀገራት በአንዱ በሕጋዊ አካልነት ስለማስመዝገብ የቀረበውን የመወያያ ሐሳብ በጥልቀት ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፎአል።

Last Updated on Thursday, 18 December 2014 23:42
Read more...
 
በጀርመን የካስል ደ/ቀ/መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አዘጋጅነት መንፈሳዊ ጉባኤ ተካሄደ። PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Friday, 08 August 2014 16:51
በጀርመን የካስል ደ/ቀ/መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አዘጋጅነት መንፈሳዊ ጉባኤ ተካሄደ።  • ከሀገር ቤትና ከአውሮፓ በተጋበዙ ሰባክያነ ወንጌል ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል።
  • “ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች ትናንትና ዛሬ“ በሚል ርዕስ ለሁለት ቀናት የቆየ ዐውደ ርዕይም በምእመናን ተጎብኝቷል።

ነሓሴ  ፳፻፮ ካስል (ጀርመን)- መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያደረጉ ጥቅሶች ከነትርጓሜያቸው በስፋት የተመሠጠሩበት የስብከተ ወንጌልና  ትምህርተ ሃይማኖት ጉባኤ በካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ተካሄደ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ፣ ደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በጀርመን የካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አዘጋጅነት ሐምሌ ፳፮ እና ፳፯ ቀን ፳፻፮ / በተካሄደው  ጉባኤ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የአካባቢውና ከሌሎችም የጀርመን ከተሞች የመጡ ምእመናን የበረከቱ ተሳታፊ ሆነዋል።

“በመንገዴ ላይ ወጥመድ አበዙብኝ“፣ “እሳቱ ከንፈርህን ነክቷልና በደልህ ተወገደ“ እና ምልክትን ተከትሎ ማመን ለክርስትናችን አደጋ ነው!በሚሉ የመጽሓፍ ቅዱስ መልእክቶች መነሻነት መጋቤ ሓዲስ ምሥጢረ ሥላሴ ማንአየህና ሊቀ ልሳናት ቀሲስ አብርሃም ዲበኩሉ ከሀገር ቤት እንዲሁምዲያቆን መስፍን ባልቻ ከቤልጂየም ሰፊና ልብ መሳጭ ትምህርት አዘል ስብከተ ወንጌል አካሂደዋል። ከምእመናን ለቀረቡ ሃይማኖት ነክ ጥያቄዎችም ሰፊ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

Last Updated on Wednesday, 13 August 2014 19:38
Read more...
 
« StartPrev12345678910NextEnd »

Page 4 of 12

Who's Online

We have 30 guests online

ሌሎች ድረ ገጾች

Featured Links:

feed-image Feed Entries


Powered by Medhanealem.