Home
Welcome to the Frontpage
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጥንታዊ መዛግብትን መሠረት ባደረጉ ጥናቶች ዋና የመረጃ ማዕከል መሆኗ ተገለጸ PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Friday, 08 August 2014 15:36

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጥንታዊ መዛግብትን መሠረት ባደረጉ ጥናቶች ዋና የመረጃ ማዕከል መሆኗ ተገለጸ


  • የጥንታዊ መዛግብት እና ቅርሶች ባለቤት የሆነችው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሃይማኖትን፣ ታሪክንና ስነ ጽሑፍን ለማጥናት ሁነኛ ምንጭ እንደሆነች ተገለጿል።
  • ለሰው ሠራሽ እና ለተፈጥሮአዊ አደጋ እየተጋለጡ ያሉ ቅርሶች ተገቢው እንክብካቤ ተጠናክሮ እንዲደረግላቸው መልእክት ተላልፏል።

ሐምሌ ፳፻፮ ዓ/ም ሐምቡርግ (ጀርመን)- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ሀገራችን እና ለመላው ዓለም ያበረከተችውና እያበረከተችው ያለው አስተዋጽዖ ቀላል እንዳልሆነ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጀርመን ሐምቡርግ ከተማ ለሦስት ቀናት በተዘጋጀ ኮንፈረንስ ላይ ገልጸዋል።

በአውሮፓ ኅብረት ድጋፍ ሰጪነት እ.ኤ.አ ከ2009 ጀምሮ ለአራት ዓመታት የቆየውና በሐምቡርግ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናቶች ማዕከል ሥር ያለው ኢትዮ-ስፔር ከልቸራል ሄሪቴጅ ኦፍ ክሪስቲያን ኢትዮጵያ- ሳልቬሽን፤ ፕሪዘርቬሽን፤ ሪሰርች የተሰኘው ፕሮጀክት መጠናቀቂያ ጊዜው መድረሱን ምክንያት በማድረግ ከጁላይ 17-19/2014 ለሦስት ቀናት በተካሄደው ኮንፈረንስ  መክፈቻ ንግግራቸውን ያሰሙት የምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ፊደልና አኃዝን፤ ጸዋትወ ዜማ በየዓይነታቸው፤ ትርጓሜ መጻሕፍት በየስልቱ፤ ስነ ጥበብንና ኪነ ጥበብን እያስተማረች ብሔራዊ ትውፊቷን የጠበቀች መሆኗ ለኢትዮጵያ ሀገራችን መመኪያ እንድትሆን አድርጓታል ብለዋል።

Last Updated on Wednesday, 13 August 2014 19:45
Read more...
 
የመንፈሳዊ ጉባዔ ጥሪ በካስል ደ/ቀ መድኃኔዓለም ቤ/ክ PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Thursday, 24 July 2014 21:09

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

“ንሥኡ ትምህርተ እምብሩር ወአእምሮ እምወርቅ = ከብር ይልቅ ትምህርትን ከወርቅም ይልቅ ዕውቀትን ያዙ“ ምሳ፰፥፲

የስብከተ ወንጌል እና ትምህርተ ሃይማኖት ጉባዔ ከሐምሌ ፳፮ እና ፳፯ ቀን ፳፻፮ / /Augest 2 & 3. 2014/ በካስል ደብረ ቀራንዮ ቤተክርስቲያን።

መርሐ ግብሩ ቅዳሜ ሐምሌ ፳፮ ቀን ፳፻፮ / ከቀኑ 8:00 ሰዓት /1400/ ላይ ተጀምሮ እሑድ ሐምሌ ፳፯ ቀን ፳፻፮ / ከቀኑ 900 /15:00/ ሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን በልዩ ልዩ አርእስት ከሚሰጡ ትምህርቶች በተጨማሪ ከምእመናን ለሚቀርቡ ጥያቄዎች በመምህራን ምላሽ የሚሰጥበት ክፍለ ጊዜ በመርሐ ግብሩ ተካቷል። በማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ንዑስ ማዕከል የተዘጋጀ ዐውደ ርዕይም ይጎበኛል።

ከሀገር ቤትና ከሌሎች አውሮፓ ሀገሮች የተጋበዙ መምህራንና ዘማርያን በማስተማርና በመዘመር ለጥያቄዎችም ምላሽ በመስጠት የሚያገለግሉ ሲሆን ያሬዳዊ መዝሙርም በመዘምራን ይቀርባል።

Read more...
 
ዓመታዊው የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓል በፈረንሳይና በኢጣሊያ ተከብሯል። PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Wednesday, 28 May 2014 20:37

ግንቦት 2006 ዓ.ም ካስል (ጀርመን) የሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል በፈረንሳይ ፓሪስ ለመጀመሪያ ጊዜ በዕለቱ በድምቀት ተከበረ።  በኢጣሊያ ባሪ ከተማም በዓሉ መከበሩን ለማወቅ ችለናል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ሚያዝያ 23/2006 ዓ.ም በፓሪስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በዓሉ የተከበረው የደቡብ ደቡብ ምስራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ በተገኙበት ነው።

በበዓሉ ዋዜማ በማህሌትና በሰዓታት የተጀመረው አገልግሎት በዕለቱም በሊቀ ጳጳሱ መሪነት የቅዳሴ ስነ ሥርዓት ተከናውኗል። በበዓሉ ከፈረንሳይ የተለያዩ ከተሞች በተጨማሪ ከጀርመንና ከቤልጂየም የሄዱ ምእመናንና ካህናት ተገኝተዋል።

በዕለቱም የፓሪስ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ጥንዶች ቅዱስ ጋብቻቸውን ፈጽመዋል።

Last Updated on Friday, 30 May 2014 12:49
Read more...
 
«እኛ እንደ ኢትዮጵያውያኑ ወንድሞቻችን ከበሮ እና ይህ ያማረ ዝማሬ የለን ይሆናል እንጂ የሃይማኖት ልዩነት ፈጽሞ የለንም።» ብፁዕ አቡነ ዩልየስ ሐና አይዲን በጀርመን የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Monday, 28 April 2014 20:44

 

ሚያዚያ 2006 (ካስል/ጀርመን) «እኛ እንደ ኢትዮጵያውያኑ ወንድሞቻችን ከበሮ እና ይህ ያማረ ዝማሬ የለን ይሆናል እንጂ የሃይማኖት ልዩነት ፈጽሞ የለንም።» ብፁዕ አቡነ ዩልየስ ሐና አይዲን በጀርመን የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ

በሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋባዥነት ከትንሣኤ በኋላ በነበረው ሰኞ፥ የማዕዶት ዕለት፥ በሐምቡርግ ከተማ የሚገኙ በክርስትና እምነት ሥር ያሉ የተለያዩ የእምነት ተቋማት ተወካዮች የክርስቶስን ትንሣኤ ምክንያት በማድረግ በአንድነት ጸሎት አድርገዋል።

ሐምቡርግ ሐርቡርግ ባለችው የቅድስት ማርያም ወቅዱስ ሽሙኒ የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የትንሣኤን በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀውን ጉባኤው በጸሎት የከፈቱት መቀመጫቸው በጀርመን ዴልመንሆርስት ከተማ የሆኑትና የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የኤኬውሜኒካል እና ከጀርመን መንግሥት ጋር ለሚደረጉ የውጭ ግንኙነት ነክ ሥራዎች በኃላፊነት ላይ ያሉት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዩልየስ ሐና አይዲን ናቸው። በመቀጠልም በዓሉን የሚመለከት መልእክት ከቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪና ከሌሎች ተወካዮች ከቀረበ በኋላ ከወንጌል የተውጣጡ ንባባት ከየቤተ እምነቱ በተወከሉ ተጋባዦች በየአገልግሎት ቋንቋቸው ለታዳሚው ተነበዋል። የሐምቡርግ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያንን በመወከል ዲያቆን ቡሩክ አሸናፊም እንዲሁ በቤተ ክርስቲያናችን የአገልግሎት ቋንቋ በሆነው በግዕዝ ከሉቃስ ወንጌል የክርስቶስን ትንሣኤ የሚያመለክት ገጸ ንባብ ያሰሙ ሲሆን የሐምቡርግ ኪዳነ ምህረት መዘምራንም በቦታው ለተገኙ እንግዶች ያሬዳዊ ዝማሬያትን አቅርበዋል።

Last Updated on Tuesday, 29 April 2014 10:36
Read more...
 
« StartPrev12345678910NextEnd »

Page 5 of 12

Who's Online

We have 22 guests online

ሌሎች ድረ ገጾች

Featured Links:

feed-image Feed Entries


Powered by Medhanealem.