Home
Welcome to the Frontpage
የትንሣኤ በዓል ዘገባ PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Monday, 28 April 2014 20:03

ሚያዚያ 2006 (ካስል/ጀርመን) የጌታችን እና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በጀርመን ባሉ በአብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት በድምቀት ተከብሯል። የጌታችንን ሕማሙን ከምናስብበት ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ በተለያዩ አድባራት ተገቢው ጸሎትም ደርሷል።

የደቡብ፣ ደቡብ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ ከጸሎተ ኀሙስ ጀምሮ በፍራንክፈረት ደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ጸሎቱን የመሩ ሲሆን በጸሎተ ኀሙስ ቅዳሴውን ከመልአከ ፀሐይ አባ ሲራክ ጋር በመሆን ከማድረሳቸውም በተጨማሪ ሥርዓት በሚያዘው መሠረት ጌታችን እና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን አብነት በማድረግ ከዕለቱ በረከት ሽተው በቤተ ክርስቲያኑ የተገኙትን ቁጥራቸው የበዛ ምእመናንን እግር የማጠቡን ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓት ፈጽመዋል። ስቅለትን እና ትንሣኤንም በዛው በቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሰጥተዋል።

Last Updated on Monday, 28 April 2014 21:20
Read more...
 
በጀርመን የበርሊን ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ከያዝነው ወር ጀምሮ ደብረ ገነት የሚል ስያሜ እንደተሰጠው ተገለጸ PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Monday, 28 April 2014 18:13

ሚያዝያ 2006 ካስል(ጀርመን) በጀርመን የበርሊን ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ከያዝነው ወር ጀምሮ ደብረ ገነት የሚል ስያሜ እንደተሰጠው ተገለጸ። የቤተክርስቲያኑም አስተዳዳሪ መልአከ ገነት የሚል የክብር ስያሜ ተሰጥቷቸዋል።

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የገዳማትና አድባራት ትክልና አመሠራረት ሥርዓትና ትውፊት መሠረት በገጠርም ይሁን በከተማ የሚገኝ እያንዳንዱ ደብር ወይም ገዳም የራሱ የሆነ መለያ ስያሜ እንዲኖረው ይደረጋል። ይህን ታሳቢ በማድረግም የደቡብ፣ ደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ የሆሣዕና በዓል ሲከበር በበርሊን ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን በመገኘት ቤተክርስቲያኑን ደብረ ገነት የሚል ስያሜ ሰጥተውታል፤ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያኑ ከዚህ በኋላ ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን በሚለው መጠሪያ ይታወቃል።

ብፁዕነታቸው አክለውም አጥቢያው የራሱ ሕንፃ ቤተክርስቲያን እንዲኖረው ከፍተኛ አመራር በመስጠት ለፍሬ እንዲበቃ በማድረግና ለበርካታ ዓመታት በሰጡት መንፈሳዊ አገልግሎት ለቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ መልአከ ገነት የሚለውን የመዐርግ ስም ሰጥተዋል። ይህንኑ ተከትሎ የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ውሳኔውን ለወረዳው ቤተክህነት፣ ካህኑ ለሚያስተዳድሯቸው ሁለት አጥቢያ አብያተክርስቲያናትና ለካህኑ በደብዳቤ አሳውቋል።

Last Updated on Monday, 28 April 2014 20:43
Read more...
 
ጥንተ መስቀሉ የሚታሰብበት ዓመታዊው የመድኃኔዓለም በዓል በጀርመን በድምቀት ተከበረ። PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Monday, 14 April 2014 15:14

 

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት ዓመታዊው የመድኃኔዓለም በዓል በጀርመን ሀገር በድምቀት ተከበረ።

ምእመናን ለካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ሕንፃ ቤተክርስቲያን መግዣ የሚውል ከ10 ሺ ዩሮ በላይ ገንዘብና የጣት ወርቆቻቸውን ለግሰዋል።

በርካታ መንፈሳዊ ቁምነገሮችን ያካተተችው ቀራንዮ መጽሔት ቅጽ ሁለትም ታትማ ለንባብ በቅታለች።

የደቡብ፣ ደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከትን ያጠናክራል የተባለለት ጠቅላላ ጉባኤም በጀርመን ካስል ከተማ ለሁለት ቀናት ተካሂዶ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

ሚያዝያ 2006 ካስል (ጀርመን)- ዓመታዊው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት በዓል ከጀርመን ከተለያዩ የአውሮፓ ከተሞችና ከካናዳ በመጡ፥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት በድምቀት ተከበረ።

በዓሉን ለማክበር ከሁሉም የጀርመን አድባራት፣ ከፈረንሳይ፣ ከስዊዘርላንድ፣ ከጣሊያንና ከካናዳ መድኃኔዓለም በረከቴን ተሳተፉ ብሎ የጋበዛቸው እንግዶች ባለፈው ሳምንት ቅዳሜና እሑድ መጋቢት 27 እና 28/ 2006 ዓ.ም የካስል ከተማን መለያችን በሆኑት የአበሻ ልብስ ነጠላና ጋቢ አጥለቅልቀዋት ነበር።

Last Updated on Monday, 14 April 2014 17:08
Read more...
 
የበዓል ጥሪ PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Friday, 28 March 2014 08:14

የበዓል ጥሪ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ። አሜን።

በጀርመን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የጌታችን እና የመድኃኒታችን የመድኃኔዓለም ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበትን ዓመታዊ በዓል ቅዳሜ መጋቢት ፳፯ እና እሑድ መጋቢት ፳፰ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም በታላቅ ዝግጅት ያከብራል።

የዘንድሮው በዓል ከቀድሞው የተለየ የሚያደርገው ደብሩ ከዚሁ ታላቅ በዓል ጋር በተያያዘ የደቡብ ደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ስብሰባን ለመጀመሪያ ጊዜ ማስተናገዱ ነው። ይህንኑ ስብሰባ ምክንያት በማድረግ የሀገረ ስብከታችንን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴን ጨምሮ በመላው ጀርመን እና በአውሮፓ ከሚገኙ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት የደብር አስተዳዳሪዎች የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ተወካዮችና ምእመናን ይገኛሉ።

Last Updated on Saturday, 29 March 2014 17:17
Read more...
 
« StartPrev12345678910NextEnd »

Page 6 of 12

Who's Online

We have 28 guests online

ሌሎች ድረ ገጾች

Featured Links:

feed-image Feed Entries


Powered by Medhanealem.