Home ዜና የአምላካችን የመድኃኔዓለም ዓመታዊ በዓል ወዕረፍቱ ለአባ መባአጽዮን በካስል ደ/ቀ/ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ።
የአምላካችን የመድኃኔዓለም ዓመታዊ በዓል ወዕረፍቱ ለአባ መባአጽዮን በካስል ደ/ቀ/ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ። PDF Print E-mail
Friday, 15 November 2019 12:30

የጌታችን የመድኒታችን የአምላካችን የመድኃኔዓለም መታዊ በዓል ወዕረፍቱ ለአባ መአጽዮን በካስል ደ/ቀ/

መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ።

በአንድ ዓመት ውስጥ አጥቢያው ለሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ግዢ ከተበደረው የባንክ እዳ ግማሹን ተመላሽ ማድረጉም ተገልጿል።


ዳር ፩- ፳፻፲፪ ዓ.ም (ካስል-ጀርመን)የዘንድሮው የጥቅምቱ መድኃኔዓለም ዓመታዊ በዓል ወዕረፍቱ ለአባ መአጽዮን

በካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የተከበረው ጥቅምት ፳፱ እና ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም ነው።


በበዓሉ ላይ ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የመጡ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ካህናት፣ ዲያቆና

እና በርካታ መናን ተገኝተዋል።


ካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ውሉደ ብርሃን እና የሐምቡርግ ደብረ መድኃኒት ኪዳነ ምሕረት መዝገበ ምሕረት ሰ/ት/

ቤቶች መዘምራንም በዓሉን የሚያዘክሩ ዝማሬዎችን በበገናና በክራር ታጅበው አቅርበዋል።


በተለይም በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በሃይማኖቱ ተከታዮች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ በማስመልከት “ኢትዮጵያ ታበጽ

እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር -- ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” እንደተባለ ስለ ቤተ ክርስቲያን፣ ስለ ሀገርና

ስለሕዝበ ክርስቲያን አምላካችን ምረቱን እንዲያወርድ በለቅሶ የታጀበ ምላም ተደርጓል።


እኔ ቅዱስ ነኝና እንደእኔ ቅዱሳን ሁኑ ዘጸ፱፪ የሚለውን የአምላካችንን ቅዱስ ቃል መረት በማድረግም በርሰ ደብር

ሩይ እስጢፋኖስና በካርልስሩኸ ምራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በቀሲስ ጌታቸው

አማካኝነትም ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል።


ገራችን አንዳንድ አካባቢዎች በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ግፍና መከራ በማውገዝም አግዚአብሔር በምሕረቱ

እንዲጎበኘን ያልተቋረጠ ጸሎት ምመኑ እንዲያደርግም መምራኑ አሳስበዋል።


የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የካስል ደ/ቀ/መድኃኔዓለምና የሐምቡርግ ደብረ መድኒት ኪዳነ ምሕረት

አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪ መጋቤ ምሥጢር ዶ/ር ኅሩይ ኤርምያስ ያ ሁሉ የስደት ጊዜ አልፎ ለዚህ በመድረሳችን

ለአምላካችን ክብርና ምስጋና ይድረሰው ብለዋል።


የደብሩን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት እንዲቻል ከባንክ በብድር ተወስዶ ከነበረው ፻፳፼ ሺ ብር ውስጥም ባለፈው አንድ

ዓመት ብቻ ግማሹ መመለሱን የገለጹት አስተዳዳሪው እንዲህ ይነት ተምር የመድኃኔዓለም ፈቃድና ይሁንታ ከሌለበት

እንዴት ይፈማል በማለትም ምመኑ አምላካችንን ደጋግሞ እንዲያመሰግን ጠይቀዋል። ቀሪውንም እዳ በአጭር ጊዜ

በማጠናቀቅ በሌሎች ከተሞች ተመሳሳይ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነፁ መላው ምመን ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም

በእግዚአብሔር ስም ጠይቀዋል።

መናኑም ጥያቄውን በመቀበል የቻሉትን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ በጭብጨባና በልልታ ቃል ገብተዋል።


ቅዳሜ ከቀኑ 10፡00 (17፡00) በዋዜማ ቁመት የተጀመረውና ማምሻውን በትምህርተ ወንጌል ሌሊቱን በማኅሌት ቀጥሎም

በቅዳሴ፣በምሕላና በዑደተ ታቦት የተከናወነው የበዓሉ መርሐ ግብር በመሳጭ ማኅሌቱ፣ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ቅኔ

በምእመናንም እልልታና ጭብጨባ ታጅቦ ን በሐሤት የሞላ ድንቅ በዓል ሆኖ አልፏል


ደብሩን በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤና በሕንፃ አሪ ማበሩ ውስጥ ለሁለት የምርጫ ያት ላገለገሉት የአመራር

አባላት የምስክር ወረቀትና የማስታወሻ ሽልማት በደብሩ አስተዳዳሪ ተበርክቷል። ምእመኑም ከመቀመጫው ተነ

ቤተ ክርስቲያኑን በቅንነት ላገለገሉት አመራሮች በእልልታና በጭብጨባ ምስጋናውን አቅርቧል።


በደብሩ አስተዳዳሪ የተዘጋጀውና የመጀመሪያው እትም ሽያጭ ሙሉ ገቢ ለቤተ ክርስቲያኑ ሕንፃ የባንክ እዳ ለመመለስ

ለሚሰባሰበው ገቢ እንዲውልም “ቅዳሴ ርባን” የተሰኘው መንፈሳዊ መጽሐፍ ለገበያ ቀርቧል። ደብሩ የሕንፃ ቤተ

ክርስቲያንባለቤት ለመሆን በመብቃቱም “ቀራንዮ መጽሔት ታትሞ በመጠነኛ ዋጋ ለምመኑ መራጨት ጀምሯል።

መናን አላማውንከማሳካት ባሻገር ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ጥንካሬ የሚጠቅሙንን መጽፍና መጽሔት በማንበብ

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና በእምነታችን ፀንተን እንድንኖርም አስተዳዳሪው አስገንዝበዋል።


በመጨረሻም ታቦተ ሕጉ ዑደት በማድረግ የበዓሉ ሥነ ርዓት በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል። የተባረከ መስተንግዶ

በመደረጉም ምመኑ ምስጋናውን አቅርቧል።

 

 

ሌሎች ድረ ገጾች

Featured Links:Powered by Medhanealem.