ግጥም
አይቴኑ ምሥራቅ? /ምሥራቅ ወዴት ትሆን?/ PDF Print E-mail
Saturday, 08 December 2012 16:35

 

 

አይቴኑ ምሥራቅ / ምሥራቅ ወዴት ትሆን ?/

ከሦስት ዓመት በፊት ትምህርት ቤት ሳለን፤

ጉዞ አዘጋጁና መምህሮቻችን፤

ወደ ደቡብ መንደር መንቀሳቀስ ጀመርን።

ወደ አመሻሹ ላይ ታንዲቱ ከተማ፤

ዕረፍት እንድናደርግ ሁሉ ሰው ተስማማ።

ተሜ እንደየምርጫው ተመራረጠና፤

በየክፍሉ ገብቶ ሲያወራ ሲዝናና።

አኀው ተሰብስበን ባንድ ላይ ሆንና፤

መጣፉን ጋቢውን ባንድ አዘጋጀንና፤

ተነሣን በኅብረት ለማድረስ ምስጋና።

ጸሎት ተቀባዩ የፀሐዩ መውጫ፤

ወዴት ይሆን ታዲያ የምሥራቅ አቅጣጫ።

Read more...
 
በእምነት ወደ አምላኩ PDF Print E-mail
Saturday, 08 December 2012 00:09

በእምነት ወደ አምላኩ

ያላንዳች ጥርጥር በአምላክ መታመን

መገለጫው ይህ ነው የበጎ ምእመን

በእምነት ወደ አምላኩ አንገቱን ያቀና

ድል ያደርጋል እንጂ አይወድቅ በፈተና፤

በኃይል በሠራዊት በሰይፍ በጦር

ፈጽሞ አይድንም የሰው ልጅ በምድር።

ግና በሃይማኖት የጸና ምእመን

ሳይገፋ ይጥላል ባላጋራውን።

ጠላት ተነሣብኝ ብለህ አትደንግጥ

ይልቅ ሀሣብህን ለአምላክህ ስጥ፤

Read more...
 
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ስለ ግእዝ ከገጠሙት PDF Print E-mail
Saturday, 08 December 2012 00:05

 

አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ስለ ግእዝ ከገጠሙት

የማናውቀውን ፊደል ሩዝ

ከሚሲዮን ቤት ስንጋበዝ

በትምህርት ወጭት በጥፈት ዳካ

በምላስ በብርዕ በቀለም መንካ

የውጭ ቋንቋ ብንፈተፍት

Read more...
 


ሌሎች ድረ ገጾች

Featured Links:

feed-image Feed Entries


Powered by Medhanealem.