Home ትምህርት
ትምህርት
ሰሙነ ሕማማት PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Tuesday, 07 April 2015 20:59

ሰሙነ ሕማማት

በመምህር ጌቱ መንክር

ሰሙነ ሕማማት የሚለው የጊዜ ስያሜ ሰሙን እና ሕማማት የሚሉ የሁለት ቃላት ጥምረት ሲሆን ሰሙን ስምንት፣ ሳምንት ፤ ሕማም ወይም በብዙ ሕማማት ማለት ደግሞ በቁሙ ሕመም ሕመሞች ፣ መከራ፣ እንግልት ማለት ነው። በጥቅሉ ሰሙነ ሕማማት ማለት የሕማም የመከራ ሳምንት ማለት ነው።  ሳምንቱ በዚህ ስያሜ የተጠራው ጌታ መዋዕለ ስብከቱን ሲፈጽም በለበሰው ሥጋ ብዙ ጸዋትወ መከራ የተቀበለበት ሳምንት በመሆኑ ነው። መከራ የተቀበለው በርግጥ ከኀሙስ ሌሊት ጀምሮ ቢሆንም በመጋቢት ፳፪ ቀን እሑድ“ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት“፤ “ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር“ በሚል የዐዋቆችና የሕፃናት ምስጋና ታጅቦ ወደ ኢየሩሳሌም ከገባ በኋላ አይሁድ በየዕለቱ የሚከሰስበትን የሚፈረድበትን በሞት የሚቀጣበትንም ምክንያት ሲፈልጉ፣ ሲመክሩና ይሙት በቃ ሊያስፈርዱበት ሲስማሙ ሲያስማሙ በመሰንበታቸው ሳምንቱ ሁሉ ጌታ ቡሩክ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውን ስለማዳን በገዛ ፈቃዱ የተቀበላቸው መከራዎቹ የሚታሰቡበት ልዩ የጸሎት፣ የስግደትና የሱባዔ ሳምንት በመሆኑ ሰሙነ ሕማማት ይባላል።

Last Updated on Tuesday, 07 April 2015 21:11
Read more...
 
ምሥጢረ ሥላሴ PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Wednesday, 26 February 2014 17:41

ምሥጢረ ሥላሴ

ሐዋርያ ወንጌል ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ “ወባሕቱ በቤተ ክርስቲያን እፈቅድ ኀምስተ ቃላተ እንግር በልብየ = ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን አምስት ቃላትን ልናገር በልቤ እሻለሁ“ ቆሮ፲፬፲፱ እንዳለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከውቅያኖስ የጠለቀውን ከነፋስ የረቀቀውን ትምህርተ ክርስትና በክቡር ደሙ ከዋጃት ከማይነጥፍ ከክርስቶስ ኢየሱስ ቃል ምንጭነት የታመኑ ባለሟሎቹ ሐዋርያት ቀድተው እንዳስረከቧት አዕማድ በተባሉ አምስት ምሥጢራት ከምላቱ ሳይጎድል ከስፋቱ ሳይጠብ እንደ ወርቅ እንክብል በጠሩ ኅብረ ቃላት ጠቅልላ ታስተምራለች። አምስት ምሥጢራት የተባሉትም

፩. ምሥጢረ ሥላሴ .  ምሥጢረ ሥጋዌ . ምሥጢረ ጥምቀት . ምሥጢረ ርባን . ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ናቸው።

ዓምድ ማለት ሙሰሶ ማለት ነው፥ አዕማድ በብዙ ፤ አዕማድ መባላቸው ሙሰሶ ቤትን ማዕበል እንዳይጥለው ነፋስ እንዳይገፋው እንደሚያጸና እኒህም ልቡናን በኑፋቄ እንዳይታወክ ከክህደት ከቀቢጸ ተስፋ እንዳይደርስ በእምነት በተስፋ የሚያጸኑ ስለሆኑ ነው። ሙሰሶ የሌለው ቤት ነፋስ ሲገፋው ይወድቃል ትምህርተ ሃይማኖትም ተምሮ ያላወቀ ሰው በጥርጥር በክህደት በሃይማኖት ከሚገኝ ጸጋና ክብር ይወጣል። ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ከሁሉ አስቀድማ ለወጣንያን ለማዕከላውያን በሚረዳቸው መጠን እኒህን ምሥጢራት ታስተምራለች። ምሥጢራት መባላቸውም ምሥጢር ለታመነ እንጂ ለሁሉ እንደማይነገር በክርስቶስ አምላክነት ወደማመን ለመጡ እንጂ በክህደት በአምልኮ ጣዖት ላሉ ለአሕዛብ ለአረማውያን የሚነገሩ ቢነገሩም በምር የሚረዱ ስላይደሉ፤ ዳግመኛም ለአእምሮ የረቀቀ ነገር ግን እውነት መሆኑ የታመነ ዕፁብ ዕፁብ ተብሎ በዕፁብ የሚወሰን በኅሊና መመራመር ግን የማይወሰን ድንቅ የሆነው ሁሉ ምሥጢር እንዲባል ሰው ዕፁብ ዕፁብ ብሎ በማመን የሚቀበላቸው እንጂ በመመራመር የማይወስናቸው ድንቅ እውነታዎች ስለሆኑ ነው።

Read more...
 
ንጽህት ዘአልባ ርስሐት! PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Tuesday, 12 August 2008 09:26

ንጽህት ዘአልባ ርስሐት!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

በመምህር ኅሩይ ኤርምያስ

በዚህ ትምህርታዊ ጽሑፍ ከጥንተ አብሶ ጋር በተያያዘ አሁን አሁን ጐላ ብሎ መሰማት የጀመረው “እመቤታችን ጥንተ አብሶ ነበረባት፤ በብስራት ጊዜ ጠፋላት” የሚል መንፈስቅዱስ ያልገለጠው መጽሐፍ ያልተናገረው ሥርዋጽ ከመሰማትና ከመነበብ አልፎትክክለኛው ኦርቶዶክሳዊ እምነትና ትምህርት’ የሚል የሃይማኖት ቡሉኮ ተደርቦለት በመለፈፉ አልፎ አልፎ ክርክርና ሙግት ሊያስነሣ መጀመሩን በመግለጽ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን ስለጥንተ አብሶ የምታምነውንና የምታስተምረውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንድገልጥላቸው በጠየቁኝ ምእመናን ጥያቄ መነሻነት ጊዜና ዕድል ገጥሟቸው የሚያነቡት ምእመናን ሁሉ ስለጥንተ አብሶ ምንነትና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ ነበረባት ወይስ አልነበረባትም? ስለሚለው ጥያቄ በቂ ዕውቀት እንዲኖራቸው በመንፈስቅዱስ ገላጭነት በመጻሕፍት ዋቢነት ሊቃውንት ካስተማሩት መምህራን ካመሰጠሩት ወስጄ ጥቂት ለማስረዳት እሞክራለሁ።

በቅድሚያ ‘ጥንተ አብሶ ምንድር ነው? የሚለውን እንመልከት

 

Last Updated on Wednesday, 21 November 2012 16:11
Read more...
 
ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Saturday, 07 July 2007 09:54
ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ
ማርቆስ የሚለው ስም ሦስት ፍቺዎች አሉት ንብ፣አንበሳ እና ካህን:: በወንጌልና በመጽሐፈ ቅዳሴ አንድምታ ትርጓሜ መጻሕፍት እንደታተተው ንብ የሚለው ፍቺ የተሰጠው ንብ አበባ ካለው ተክል ሁሉ ቀስማ ማር እንድትሠራ እርሱም ቀድሞ ከጌታ ኋላም ከጌታ የተማርኩት ይበቃኛል ሳይል ከሐዋርያት ተምሮ ደገኛይቱን ወንጌልን በማስተማሩና በመጻፉ ሲሆን አንበሳ መባሉ አንበሳ እንስሳት አራዊትን በክርኑ እንዲሰብር በግብጽ ይመለኩ የነበሩ በእንስሳ አምሳል የተሠሩ ጣዖታትን በወንጌል ቃል ኃይልነት በማጥፋቱ ነው:: ካህን የሚለው ትርጉም ደግሞ በሐዋ 14:13 “ወአምጽኡ ማሬ ዘድዮስ” ተብሎ ከተመዘገበው መጽሐፍቅዱሳዊ አሳብ የተወረሰ ነው::
Last Updated on Wednesday, 21 November 2012 12:11
Read more...
 


ሌሎች ድረ ገጾች

Featured Links:

feed-image Feed Entries


Powered by Medhanealem.